የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ 34 ከመቶ ደርሷል
(ጥላሁን ካሳ) የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ዋና ስራዎች ክረምቱ ከመጠናከሩ በፊት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው አለ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን። ኮርፖሬሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገረው በዚህ አመት ይጠናቀቃል ከተባለው 40 በመቶ ስራ እስከ ግንቦት መጨረሻ 34 ከመቶ በላይ የሚሆነው ተከናውኗል። የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ከሚያልፍባቸው ቦታዎች መካከል በዋነኛነት ጊዮርጊስ አካባቢ በሚገኘውን … Read more
ቤኒሻንጉል:- 28 ሀላፊዎች ዜጎችን በማፈናቀል ተጠርጥረው ታሠሩ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ያሶ ወረዳ የሚኖሩ የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆችን ያለአግባብ አፈናቅለዋል ተብለው የተጠረጠሩ 28 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጋዎ ጃኔ ትናንት እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ ካለፈው እሁድ ጀምሮ የተያዙት በቅርቡ በያሶ ወረዳ ለረጅም ዓመታት የኖሩ የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆችን በማፈናቀል ወንጀል ተጠርጥረው ነው፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት 28 … Read more
ቤኒሻንጉል:- በዜጎች መፈናቀል ሳቢያ የም/ቤት አባላት ታሠሩ
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ካማሽ ዞን በዜጎች መፈናቀል እጃቸው አለበት የተባሉ ኃላፊዎች ያለመከሰስ መብት መነሳቱን ፋና እና የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለጹ፡፡ ******* ፋና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት ትናት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በክልሉ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት ናቸው ያላቸውን 2 የምክር ቤት አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ። ያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር ውለው በህግ … Read more
ፌዴሬሽን፡- ለዋልያዎች መቀጣት መንስኤው ‹ዝንጋታ› ነው
(ሰይፉ አለምሰገድ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምንያህል ተሾመ ሁለት ቢጫ ካርድ አይቶ ሳለ ሰኔ 1/2005 ከቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን ጋር በተደረገው ጨዋታ መሰለፉ ስህተት እንደሆነ አመነ፡፡ ፌዴሬሽኑ ብሄራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ከመጫወቱ በፊት ችግር ስለመፈጠሩ ፊፋ አሳውቆት እንደነበር ገልጿል፡፡ ሆኖም ይህ ችግር በቡድኑ ተጫዋቾችና በደጋፊዎች ላይ ያልተፈለገ የመንፈስ ጫና እንዳይፈጥር በመስጋት መረጃውን ይፋ ሳያደርግ … Read more
ስለሕዳሴ ግድብ፡- የ‹አንድነት› ፓርቲ መግለጫ [ሙሉ ቃል]
ባለፈው ዓርብ ‹አንድነት› ፓርቲ ስለሕዳሴ ግድብ የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ ኢቲቪ ያተመውን ዜና እዚህ ብሎግ ላይ ደግመን ማተማችን ይታወሳል፡፡ የፓርቲውን ሙሉ መግለጫ ዛሬ ያገኘን ሲሆን፣- ከኢቲቪ በወሰድነው ዜና ላይ ከቀረበው ጋር ትርጉም ያለው ልዩነት ባይኖረውም የ‹አንድነት› ፓርቲ ደጋፊ የሆኑ አንባቢዎቻችን ባቀረቡት ቅሬታ ምክንያት የመግለጫውን ሙሉ ቃል አትመነዋል፡፡ ለቀጣይ ግን እኛን ከመተቸት ይልቅ ፓርቲያቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲጠራ … Read more
ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ ዙር አለፈች
ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ ዙር አለፈች፡፡ የሀገር ውስጥ ሚዲያ እንደሚከተለው ዘግቦታል፡፡ ********* ፋና ለብራዚሉ የ2014 አለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድቡን በ10 ነጥብ እየመራ ያለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከተከታዩ የደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ተጫውቶ 2 ለ 1 አሸነፈች ። በጨዋታው ባፋና ባፋናዎቹ ቀድመው ጎል ቢያገቡም ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ኢትዮጵያ በጌታነህ ከበደ አቻ ሆና ነበር ። አንድ … Read more
ኢሕአፓ፡- መንግሥት በህዳሴ ግድብ ሰበብ ‘ግብጽን እየተነኮሰ’ ነው
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሰኔ 4 ቀን 2005 ዓ.ም. የወያኔ አገዛዝ ሕዝብን ለጦርነት፤ ሀገርን ለጥቃት እያዘጋጀ ነው የወያኔ አገዛዝ የሕዝብን ትኩረት መደረግ ካለበት ወሳኝ ትግል ለመነጠል ሲያደርገው የነበረውን ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ በተመክሮ የተገነዘበው ነው። በቅርቡ ደግሞ ህዳሴ ግድብ በሚለው ማታለያ የለመደባቸውን ተላላዎች በዙሪያው እያሰለፈና ሕዝብንም እየዘረፈ ያለው አልበቃ ብሎት ግብጽን እየተነኮስና እየቀሰቀስ በመቀጠሉ … Read more
ሰማያዊ ፓርቲ:- ግድቡ ‘ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚደለቅ ከበሮ’ ነው
በመሠረቱ በአባይ ወንዝ ላይ የተጀመረው ግድብ ከሐገራዊ ጠቀሜታው ይልቅ የገዥውን ፓርቲ የስልጣን እድሜ ለማራዘም የታለመና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚደለቅ ከበሮ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ የግድቡ ሥራ የገዥውን ፓርቲ የተለየ አሣቢነትና ተቆርቋሪነት የሚያሳይ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው ልፈፋ ከተራ ጩኸት በዘለለ የዜጎችን ልብ የሚያማልል አይደለም፡፡
‘አንድነት’ ፓርቲ፡- የሕዳሴ ግድብ ባለቤት አልተለየም (+video)
(ከበደ ካሳ) አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የኢትዮጵያ መንግስት የአባይን ጉዳይ የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረጉን እንዲያቆም አሳሰበ፡፡ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) “ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የቆረጠ ፓርቲ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ መጣሉ የማይቀር ነው” በሚል ርዕስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንደገለፁት አባይ ከመገደቡ በፊት መፈፀም የሚገባው የዲፕሎማሲ ስራዎች አልተሰሩም፡፡ “በአባይ … Read more
መንግስት፡- “የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል”
* በግብፅም ሆነ በሌላ ማንኛውም ወገን የሚቀርብ የግድቡን ግንባታ የማዘግየት ወይንም ከነአካቴው የማቋረጥ ነገር ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም * በሕዳሴው ግድብ ሽፋን የውስጥ ችግርን ለማቃለል የሚደረገው ጥረትም የግብፅን ዘላቂ ጥቅም አይጠብቅም – የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል” በሚል ርዕስ … Read more